የእስልምና ሃይማኖት

ቁርኣን እና ከሰዎች ሁሉ ምርጥ የሆኑት ነብይ ሓዲሦች እንደገለፁት

 ሙሐመድ የአላህ መልእክተኛ ናቸው።

በመሐመድ ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም መልእክተኝነት ማመን – ከእስልምና መሠረታዊ ምሰሶዎች ሁለተኛው ክፍል እና ዲነል ኢስላምም የተገነባበት ዋነኛው መሠረት ነው።

የትኛውም ግለሰብ ሙስሊም የሚሆነው በሁለቱ የምስክርነት ቃላቶች ሸሃዳ ከሰጠ ነው። ይኸውም ከአላህ በስተቀር ሌላ በእውነት የሚመለክ አምላክ እንደሌለ እና ሙሐመድም የአላህ መልእክተኛ መሆናቸውን በመመስከር ነው።

ሀ- የመልእክተኛው ትርጉም ምንድን ነው? ሙሐመድስ ማን ናቸው? ከእርሳቸውስ ሌላ መልክተኞች አሉን?

በእነዚህ ገፆች ውስጥ ለመመለስ የምንሞክረውም ይህንኑ ነው።

የአላህ መልእክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይሁን) በንግግራቸው እውነተኝነት እና በመልካም ስነ-ምግባራቸው ከፍተኛ ደረጃ ላይ የደረሱ ሲሆን፤ አላህ ከሰዎች መካከል የመረጣቸው እና ከሃይማኖታዊ ትእዛዛት ወይም ከሩቅ ምስጢር ጉዳዮች የሻውን ገልጦላቸው ለሰዎች ለማድረስ በተልእኮ የሚመርጣቸው ናቸው። በመሆኑም ለሰዎች የተላኩ የአላህ መልእክተኛ ሰው ናቸውና እንደማንኛውም ሰው ናቸው፤ ሰዎች እንደሚበሉት ይበላሉ፣ እንደሚጠጡት ይጠጣሉ፣ የሰው ልጅ የሚያስፈልገው ነገር ሁሉ ያስፈልጋቸዋል። ከእነርሱ የሚለዩት ታዲያ ከአላህ ዘንድ በሚመጣላቸው ወሕይ (የሚገለጥላቸው መለኮታዊ ራእይ) ነው። ይኸውም ስለ ሩቅ ምስጢርም ይሁን ሃይማኖታዊ ሥርዓቶች ያሳውቃቸውን ለሰዎች ያደርሳሉ። በተጨማሪም አላህ ለእርሳቸው በከባድ ኃጢዓት ላይ ከመውደቅ እንዲሁም የአላህን መልእክት ለሰዎች ከማስተላለፍ በሚጥስ ጉዳይ ላይ ከመውደቅ ባለው ጥበቃም ይለያቸዋል።

ከሙሐመድ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይሁን) በፊት የነበሩትንና ከቀደሙት መልእክተኞች ታሪኮች መካከል ጥቂቶቹን እናቀርባለን። የመልእክተኞች ተልእኮ አንድ መሆኑንና ይኸውም አላህን በብቸኝነት እንድናመልከው የተደረገ ጥሪ መሆኑ ግልፅ እንዲሆንልን ይረዳናል። ስለ ሰው ልጆች አጀማመር ታሪክ እና ሰይጣን የሰው ልጆች አባት ለሆኑት አደምና ለዝርዮቹ ያለውን ጠላትነት በመቃኘት እንጀምራለን።

ለ – ከመልክተኞች የመጀመሪያው የሆኑት አባታችን አደም (የአላህ ሰላም በእርሳቸው ላይ ይሁን)፡-

About The Author

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው