ውድ አንባቢ ሆይ፡-
ይህ እጆ ላይ የሚገኘው መጽሐፍ ቀለል ባለና ሁሉንም ገፅታዎች (እምነቱን – አዳቦቹን – ህግጋትን – ሁሉንም ትምህርቶቹን) ባካተተ መልኩ ከእስልምና ሀይማኖት ጋር ያስተዋውቆታል።
በርካታ ዋና ዋና ነገሮች ግምት ውስጥ ለማስገባት ሞክሬያለሁ፦
አንደኛ: ሃይማኖቱ የተመሰረተበትን መሰረተ‐ሃይማኖቱ ላይ ማተኮር።
ሁለተኛ፡- በተቻለ መጠን አጠር ማድረግ።
ሶስተኛ፦ አንባቢው በቀጥታ የእስልምና ዋና ምንጮች ፊት ለፊት ሆኖ መመሪያውንና አስተምህሮቱን ይጎነጭ ዘንድ፥ እስልምናን ከመነሻ ምንጮቹ (ከተከበረው ቁርኣን እና ከመልእክተኛው የአላህ ሰላት እና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይሁን ሀዲስ) በማቅረብ።
ውድ አንባቢ ልክ መፅሀፉን እንዳጠናቀቅክ ራስህን ስለ እስልምና ሀይማኖት ግልጽ የሆነ ምልከታ ኖሮህ ታገኘዋለህ። ከዚያም በሂደት ስለዚህ ሀይማኖት ያለህን የእውቀት ድልብ ታሳድግበታለህ።
ይህ በእጅዎ የሚገኘው መጽሐፍ በዋነኛነት የእስልምናን ሀይማኖት ለመቀበል እና እምነቱን፣ ሥርዓቱን እና ፍርዱን መማር ለሚፈልጉ ሰዎች በግምባር ቀደምነት ብሎም ከዛም በላይ ላሉ በረካታ ማህበረሰብ አንገብጋቢ ነው።
በተጨማሪም ስለ ሀይማኖቶች ለማወቅ ፍላጎት ላላቸው በተለይም በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች ስለተቀበሏቸው ሀይማኖቶች ማወቅ ለሚፈልጉ እንዲሁም ለእስልምና ጥሩ ቀረቤታ ላላቸውና በእስልምና አንዳንድ ነገሮች አድናቂዎች እና ምናልባትም ባለማወቃቸው የእስልምና ጠላቶችና ኢስላም ጠል ለሆኑ ለእስልምና ጠላቶች እና ተቃዋሚዎቹ ታሳቢ አድርጎ የተዘጋጀ ነው።
በዚህ መጽሐፍ ላይ በከፍተኛ ሁኔታ ታሳቢ ከተደረጉ መካከል የእስልምናን ሀይማኖት ለሰዎች ለማስረዳት የሚፈልጉ ሙስሊሞችም ተጠቃሽ ናቸው። ይህ መጽሐፍ ጥረታቸውን የሚያሳጥርላቸው እና ስራቸውንም የሚያቀልላችው ይሆናል።
እናም ውድ አንባቢ ሆይ! ስለ እስልምና ሀይማኖት መነሻ የሚሆን ጠቅላላ እውቀት ከሌለህ በዚህ መፅሃፍ ውስጥ የተካተቱትን ትርጉሞች ለማወቅ ከፍተኛ ትኩረት እና ጥንቃቄ የተሞላበት ንባብ እንደሚያስፈልግህ ተረዳ። እንዲህ ስለተባልክ ደሞ አትሰላች። ለጥያቄዎችህ መልስ የሚሰጡ ብዙ ኢስላማዊ ድረ-ገጾች ስላሉልህ ማለት ነው።