የእስልምና ሃይማኖት

ቁርኣን እና ከሰዎች ሁሉ ምርጥ የሆኑት ነብይ ሓዲሦች እንደገለፁት

ለ- አላህ ለምን ፈጠረን?

የዚህ ትልቅ ጥያቄ መልስ እጅግ በጣም አንገብጋቢ ነው። ይሁን እንጂ መልሱን ከወሕይ (ከመለኮታዊ መገለጥ) ማግኘት ግድ ነው። ምክንያቱም የፈጠረን አላህ ነውና እኛን የፈጠረበትን ዓላማ የሚነግረንም እርሱ ነውና። ልዑሉ አላህ እንዲህ ብሎናል፡-

“ጋኔንንና ሰውንም ሊግገዙኝ እንጅ ለሌላ አልፈጠርኳቸውም።”

[አዝ-ዛሪያት፥56]

ስለዚህም ባሪያነት (አምልኮ) ተቆጥረው የማይዘለቁትን ፍጡራን ሁሉ የሚያካልል መገለጫ ነው። የተከበሩት ፍጥረታትም (መላእክት) ይሁኑ ሌሎቹም እስከ ብርቅዬ ድንቅ ፍጡራኖችም ጭምር ህይወታቸውን ለአምልኮና የዓለማቱ ጌታ አላህን ለማወደስ የተመቻቹ ሆነው ነው የተፈጠሩት።

{ሰባቱ ሰማያትና ምድርም በውስጣቸውም ያለው ሁሉ እርሱን ያልቃሉ። ከነገርም ሁሉ ከማመስገን ጋር የሚያልቀው እንጂ አንድም የለም፡፡ ግን ማላቃቸውን አታውቁትም። እርሱ ታጋሽ መሓሪ ነው።}

[አል_ኢስራእ፥ 44]

ልክ የሰው ልጆች ለእስትንፋስ እንደተገሩት ሁሉ መላእክቶችም አላህን ለማወደስ የተገሩ ናቸው።

ነገር ግን የሰው ልጅ ለፈጣሪው ያለው ተገዥነት በውዴታ እንጂ በግዴታ ላይ የተመሰረተ አይደለም። (ውዴታ እና ግዴታ)

{እርሱ ያ የፈጠራችሁ ነው፤ ከእናንተም ከሓዲ አልለ፤ ከእናንተም አማኝ አልለ፤ አላህም የምትሠሩትን ሁሉ ተመልካች ነው።}

[አተ_ተጋቡን፥ 2]

{አላህ በሰማያት ያለው ሁሉ፣ በምድርም ያለው ሁሉ፣ ፀሐይና ጨረቃም፣ ከዋክብትም፣ ተራራዎችም፣ ዛፎችም፣ ተንቀሳቃሾችም ከሰዎች ብዙዎችም፣ ለርሱ የሚሰግዱለት መሆኑን አታውቁምን ብዙውም በርሱ ላይ ቅጣት ተረጋገጠበት። አላህ የሚያዋርደውም ሰው ለእርሱ ምንም አክባሪ የለውም። አላህ የሻውን ይሠራልና።}

[አል_ሓጅ፥18]

አላህ የፈጠረን እርሱን እንድናመልከው እና ይህንን አምልኮ በማሳካቱ ረገድ ያለንን ስኬታማነት ሊፈትነንም ነው። በዚህም መሰረት አላህን የሚያመልክ፣ የሚወድ፣ የሚግገዛ፣ ትእዛዙንም የሚፈጽም እና ከተከለከለው የሚርቅ ሰው የአላህን “ሪዷ” (ወዶ መቀበሉን)፣ እዝነቱን እና ውዴታውንም ያገኛል፤ በመልካሙም ይመነዳዋል።

የፈጠረውንና ሲሳይ የሚለግሰውን ጌታ ተመላኪነት ያልተቀበለ፤ ከአምልኮም የሚኮራ፤ ለአላህ ትእዛዛትና ክልከላ ማጎብደድን ያልተቀበለ የአላህን ቁጣና በቀል እንዲሁም አሳማሚ ቅጣቱን ነው የሚያተርፈው። ጥራት ይገባውና የላቀው አላህ በከንቱ አልፈጠረንም በከንቱም አልተወንም። እጅግ ድንቁርናቸውና ክፉነታቸው ከበረታባቸው ሰዎች መካከል አንዱ ወደዚህ ዓለም ወጥቶ የመስማት፣ የማየትና የማመዛዘን ችሎታም ተሰጥቶት ከዚያም ጊዜያቶችን ቆይቱ ወደ ዱኒያ የመጣበትን ምክንያትም ይሁን ወደ የትስ እንደሚሄድ ሳያውቅ የሞተ ነው። የላቀው አላህ እንዲህ ብሏል፦

{«የፈጠርናችሁ ለከንቱ መኾኑን እናንተም ወደኛ የማትመለሱ መኾናችሁን ጠረጠራችሁን» (ለከንቱ የፈጠርናችሁ መሰላችሁን)}

[አል-ሙእሚኑን: 115]

አላህ ዘንድ ከኛ መካከል በእርሱ ያመነ፣ መመኪያው አላህን ያደረገ፣ ወደርሱም የተፋረደ፣ የወደደ፣ ጥልቅ ክብርንም የሰጠ፣ በአምልኮ ወደ እርሱ እየተቃረበ በሁሉም ቦታ የአላህን ደስታ የሚፈልግ የሆነ ሰው እና ፈጥሮ የቀረፀውን ጌታውን የሚክድ፣ በአንቀፆቹ እና በሃይማኖቱም የሚያስተባብል ለአላህ ማጎብደድንም የማይቀበል የሆነ ሰው እኩል አይደለም።

የመጀመሪያው መከበርን፣ መልካም ምንዳን፣ መወደድን እና ስራው ተቀባይነትን የሚያገኝ ሲሆን፤ ሌላኛው ደግሞ በቀልን፣ ቁጣን እና ቅጣትን ነው የሚያገኘው።

ሰዎች ሞተው ከተቀበሩ በኋላ አላህ ከመቃብራቸው አስነስቶ ከነሱ መካከል በጎ ያደረገውን በጀነት ፀጋው ውስጥ ደስታን እና ክብርን የሚያጎናፅፍበት እና አላህን ያመፀውን ትዕቢተኛ ደግሞ በጀሀነም የቅጣቱ ሀገር የሚቀጣበት ነው።

እስኪ የበጎ አድራጊ ክብር እና መልካም ምንዳ ታላቅነትን አስበው ይህ ሽልማት እና ክብር ከአለም ከተብቃቃውና ቸር ከሆነው አምላክ ሲሆን ያም ልግስና እና እዝነቱ ገደብ የለሽ እንዲሁም ሀብቱም ከማያልቀው ጌታ መሆኑን ደሞ አስበሀዋል?! ይህም መልካም ምንዳ የማያልቅ እና የማያቋርጥ የፀጋ ጥግ ይሆናል (ይህን ደግሞ ወደ ኋላ የምናወራበት ይሆናል)። ልክ እንደዚሁ ካፊር የሚጠብቀውን ብርቱና ከባድ የስቃይ ቅጣትም ማሰብ ይኖርብሀል። ይህም ሁሉን አሸናፊ፣ ታላቅና ኩሩ ከሆነው ኩራትና ኃያልነቱ ገደብ የሌለው ከሆነው አምላክ የመጣ ቅጣት ነው።

About The Author