የእስልምና ሃይማኖት

ቁርኣን እና ከሰዎች ሁሉ ምርጥ የሆኑት ነብይ ሓዲሦች እንደገለፁት

ሐ- ኑሕ (የአላህ ሰላም በእርሳቸው ላይ ይሁን)፡-

በእርሳቸውና በአደም መካከል አሥር ክፍለ ዘመናት ነበሩ። አላህም ኑሕን ወደ ጠመሙትና ከአላህ ውጭ ጣኦታትን ማምለክ ወደ ጀመሩት ህዝቦቸው ላካቸው። ግኡዝ አካላትን፣ ድንጋይን፣ መቃብሮችንም ያመልኩ ነበር። እጅግ ገናና ከሆኑ ጣኦቶቻቸው መካከል ወድ፣ ሱዋዕ፣ የጉስ፣ የዑቅ እና ነስር የሚባሉ ነበሩ። አላህም ለአላህ ብቻ አምልኮ እንዲያደርጉ ያዟቸው ዘንድ ኑሕ (የአላህ ሰላም በእርሳቸው ላይ ይሁን) ላካቸው። ልክ የላቀው አላህ በተከታዩ የቁርአን አናቅፅ እንደነገረን ማለት ነው፦

{ኑሕን ወደ ወገኖቹ በእርግጥ ላክነው። አላቸውም፡- «ወገኖቼ ሆይ! አላህን ተገዙ። ለእናንተ ከርሱ ሌላ ምንም አምላክ የላችሁም። እኔ በእናንተ ላይ የከባድ ቀንን ቅጣት እፈራላችኋለሁ።»}

[አልአዕራፍ 59]

ህዝባቸውን አላህን ብቻ እንዲያመልኩ ጥሪ በማድረጉ ላይ ለረጅም ጊዜ ቀጠሉ። ይሁን እንጅ ከእርሳቸው ጋር ጥቂት ብቻ ነበሩ ያመኑት። ስለዚህም ኑሕ ጌታቸውን እንዲህ ሲሉ ተጣሩ፦

{(ስለ ተቃወሙትም) «አለ ጌታዬ ሆይ! እኔ ሌሊትም ቀንም ሕዝቦቼን ጠራሁ።}

{«ጥሪየም መሸሽን እንጅ ሌላ አልጨመረላቸውም።}

{«እኔም ለእነርሱ ትምር ዘንድ (ወደ እምነት) በጠራኋቸው ቁጥር ጣቶቻቸውን በጆሮዎቻቸው ውስጥ አደረጉ። ልብሶቻቸውንም ተከናነቡ። (በመጥፎ ሥራቸው ላይ) ዘወተሩም። (ያለ ልክ) መኩራትንም ኮሩ።}

{«ከዚያም እኔ በጩኸት ጠራኋቸው።}

{«ከዚያም እኔ ለእነርሱ ገለጽኩ። ለእነርሱም መመስጠርን መሰጠርኩ}

{«አልኳቸውም፡- ጌታችሁን ምሕረትን ለምኑት። እርሱ በጣም መሐሪ ነውና።}

{«በእናንተ ላይ ዝናምን ተከታታይ አድርጎ ይልካል።}

{«በገንዘቦችና በልጆችም ይለግሰላችኋል። ለእናንተም አትክልቶችን ያደርግላችኋል። ለእናንተም ወንዞችን ያደርግላችኋል።»}

{ለአላህ ልቅናን የማትሹት ለእናንተ ምን አላችሁ?}

{በልዩ ልዩ ኹኔታዎች በእርግጥ የፈጠራችሁ ሲኾን።}

[ኑሕ፡ 5_14]

ከዚህ ሁሉ ያልተቋረጠ እና አስደናቂ ጥሪ፤ ህዝባቸውንም ለመምራት ካላቸው ከፍተኛ ጉጉት ጋር ለጥሪያቸው ምላሽ የሰጡት ግን በክህደት፣ በመሳለቅ እና በእብደት በመወረፍ ብቻ ነበር።

የዛኔ እንዲህ በማለት አላህ ዋሕዩን አወረደለት፦

{ወደ ኑሕም እነሆ «ከሕዝቦችህ በእርግጥ ካመኑት በስተቀር (ወደፊት) አያምኑም። ይሠሩትም በነበሩት (ክህደት) አትዘን ማለት ተወረደ።»}

[ሁድ፡ 36]

ያመኑትን ተከታዮቻቸውን ሁሉ የሚጭኑበት መርከብ እንዲሠሩ ትእዛዝን አስተላለፈላቸው።

{ከወገኖቹም መሪዎቹ በእርሱ አጠገብ ባለፉ ቁጥር ከእርሱ እየተሳለቁ መርከቢቱን ይሠራል። «ከእኛ ብትሳለቁ እኛም እንደተሳለቃችሁብን ከናንተ እንሳለቅባችኋለን» አላቸው።}

{«የሚያዋርደው ቅጣት የሚመጣበትን በእርሱም ላይ ዘውታሪ ቅጣት የሚሰፍርበት ሰው (ማን እንደ ሆነ) ወደፊት ታውቃላችሁ» (አላቸው)።}

{ትእዛዛችንም በመጣና እቶኑም በገነፈለ ጊዜ «በእርሷ ውስጥ ከየዓይነቱ ሁሉ ሁለት ሁለት (ወንድና ሴት) ፤ ቤተሰቦችህንም ቃል ያለፈበት ብቻ ሲቀር ያመነንም ሰው ሁሉ ጫን» አልነው። ከእርሱም ጋር ጥቂቶች እንጂ አላመኑም።}

{«መሄዷም መቆሟም በአላህ ስም ነው እያላችሁም በውስጧ ተሳፈሩ. ጌታ መሓሪ አዛኝ ነውና» አላቸው.}

{እርሷም እንደ ተራራዎች በሆነ ማዕበል ውስጥ በእነርሱ (ይዛቸው) የምትንሻለል ስትሆን (በአላህ ስም ተቀመጡባት)። ኑሕም ልጁን ከመርከቢቱ የራቀ ሆኖ ሳለ «ልጄ ሆይ! ከኛ ጋር ተሳፈር ከከሓዲዎቹም አትሁን» ሲል ጠራው።}

{(ልጁም) «ከውሃው ወደሚጠብቀኝ ተራራ እጠጋለሁ» አለ። (አባቱም)፡- «ዛሬ ከአላህ ትዕዛዝ ምንም ጠባቂ የለም (እርሱ) ያዘነለት ካልሆነ በቀር» አለው። ማዕበሉም በመካከላቸው ጋረደ። ከሰጣሚዎቹም ሆነ።}

{ተባለም፡- «ምድር ሆይ! ውሃሽን ዋጪ። ሰማይም ሆይ (ዝናብሽን) ያዢ። ውሃውም ሰረገ። ቅጣቱም ተፈጸመ። ጁዲይ በሚባልም ተራራ ላይ (መርከቢቱ) ተደላደለች። ለከሓዲዎችም ሰዎች ጥፋት ተገባቸው (ጠፉ)» ተባለ።}

{ኑሕም ጌታውን ጠራ። አለም «ጌታዬ ሆይ! ልጄ ከቤተሰቤ ነው። ኪዳንህም እውነት ነው። አንተም ከፈራጆች ሁሉ ይበልጥ ዐዋቂ ነህ።»}

{(አላህም) «ኑሕ ሆይ! እርሱ ከቤተሰብህ አይደለም፤ እርሱ መልካም ያልሆነ ሥራ ነው፤ በርሱ ዕውቀት የሌለህንም ነገር አትጠይቀኝ፤ እኔ ከሚሳሳቱት ሰዎች እንዳትሆን እገስጽሀለሁ» አለ።}

{«ጌታዬ ሆይ! በእርሱ ለእኔ ዕውቀት የሌለኝን ነገር የምጠይቅህ ከመሆን እኔ ባንተ እጠበቃለሁ። ለእኔም ባትምረኝና ባታዝንልኝ ከከሳሪዎቹ እሆናለሁ» አለ።}

{«ኑሕ ሆይ! ከእኛ በሆነ ሰላም ባንተ ላይና አንተም ጋር ባሉት ሕዝቦች (ትውልድ) ላይ በሆኑ በረከቶችም የተጎናጸፍክ ሆነህ ውረድ። (ከእነሱው ዘሮች የሆኑ) ሕዝቦችም በቅርቢቱ ዓለም በእርግጥ እናስመቻቸዋለን። ከዚያም ከኛ የሆነ አሳማሚ ቅጣት ይነካቸዋል» ተባለ።}

[ሁድ፡ 38_48]

About The Author