የእስልምና ሃይማኖት

ቁርኣን እና ከሰዎች ሁሉ ምርጥ የሆኑት ነብይ ሓዲሦች እንደገለፁት

ሐ‐ ከሓራም ነገሮች ተውባ ማድረግ

እነዚህ ከፍ ብለን የጠቀስናቸው አበይት ወንጀሎችና ክልከላዎች ናቸው። ማንኛውም ሙስሊም በእነርሱ ውስጥ እንዳይወድቅ ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ አለበት። እያንዳንዱ ሰው ሲሰራው በነበረው ስራ ሁሉ መልካም ከነበረ በመልካምነቱ መጥፎ ከነበረ ደግሞ በመጥፎነቱ በትንሳኤ ቀን ምንዳውን ያገኛል።

የትኛውም ሙስሊም ከእነዚህ ክልከላዎች ውስጥ በአንዱ እንኳ ቢወድቅም ፈጥኖ ይጸጸት በተውባ ወደ አላህ ይመለስና ምህረትንም ይለምነው። ተውባው የምር እስከሆነ ድረስ ደግሞ ድጋሚ ወደ ወንጀሉ መመለስ የለበትም፤ ይልቁን በሰራው ነገር መፀፀት፤ ድጋሚ ላይመለስ ቁርጥ አድርጎ መወሰን ነው ያለበት። ምናልባት የበደለው አካል ከነበረ ደግሞ ከቻለ የበደለበትን መመለስ አለዚያ ደግሞ የተበዳዩን ይቅርታ መጠየቅ አለበት። የዚህኔ ተውባውም የምር ተውባ ይሆንለታል፤ አላህም ተውባ ባደረገበት ጉዳይ ላይቀጣው መሀርታውን ይለግሰዋል፤ ከኃጢአቱ ተውባ ያደረገ ኃጢአቱም ላይ እንዳልወደቀ ነውና።

እናም የአላህን ምህረት አብዝቶ መጠየቅ አለበት። ይልቁንም እያንዳንዱ ሙስሊምም ለሚያውቃቸው ትንንሽም ይሁን ትላልቅ ስህተቶቹ አብዝቶ የአላህን መሀርታ መጠየቅ አለበት።

{«አልኳቸውም፡- ጌታችሁን ምሕረትን ለምኑት። እርሱ በጣም መሐሪ ነውና።}

[ኑሕ፡ 10]

አዘውትሮ ምህረትን መጠየቅ እና ወደ አላህ መመለስ የምርጥ ሙእሚኖች ባህሪ ነው። የላቀው አላህ እንዲህ ብሏል፡-

{በላቸው «እናንተ በነፍሶቻችሁ ላይ ድንበር ያለፋችሁ ባሮቼ ሆይ! ከአላህ እዝነት ተስፋ አትቁረጡ። አላህ ኃጢኣቶችን በመላ ይምራልና። እነሆ እርሱ መሓሪው አዛኙ ነውና።}

{«ቅጣቱም ወደእናንተ ከመምጣቱና ከዚያም የማትርረዱ ከመኾናችሁ በፊት ወደ ጌታችሁ (በመጸጸት) ተመለሱ። ለእርሱም ታዘዙ።}

[ዙመር፡ 53 _ 54]

About The Author